Teya Salat
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

App full proxy-5.php 28

የረመዷንን ወር እንዴት እንቀበለው?


App full proxy-5.php 29
10346300 495922610509091 5902302763179697355 n

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸውና በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

ወራት አልፎ ወራት ሲተካ ተወዳጅ እና ታላቅ የሆነው የሚልዮኖች እንግዳ ሸኽሩ ረመዷን በድጋሜ ብቅ ይላል። በዚህ ወቅት ሙስሊሞች እንግዳውን ሲቀበሉ ውስጣቸው በሐሴት(በደስታ) ይሞላል። ላለመደው ሰው ሙስሊሞች ከዚህ በፊት ተገናኝተውት የማያውቁ ሊመስለው ይችላል።

ለዚህ እንግዳ ካለን ውዴታና እንግዳውን ለማስተናገድ ካለን ጉጉት የተነሳ የዕለት ተዕለት ተግባራችን እና የዘወትር ልማዳችን ይቀየራል። በሚያስገርም ሁኔታ መስጅዶች በአሏህ ባሪያዎች ይሞላሉ፤ የቁርአን ምዕራፎችም በእንባ ታጅበው ይነበባሉ።

ይህ ልዩና የተባረከ የሆነ ወር ለማክበር ብዙ መስዋዕቶችን እንከፍላለን። ታዲያ የዚህ ወር ተልዕኮ መረዳት እንዴት ይሳነናል?

አብዛዋቻችን የረሳነው ነገር ቢኖር ይህ ታላቅ እንግዳ ብዙና ጥልቅ የሆኑ አላማዎች ፣ ኒዕማዎች ፣ ሃላፊነቶች አካበውት እና አጅበውት የመጣ መሆኑ ነው።

እንግዳው ወደ ቤታችን ሊመጣ በጉዞ ላይ በሆነ ጊዜ እንግዳውን ለመቀበል ሽርጉድ እንላለን፤ ምንጣፎቻችነን ፣ ብፌዎቻችነን ፣ የአልጋችነን ስር ፣ መስታውቶቻችነን ፣ ልብሳችነን ባጠቃላይ ቤት ደጁን ማለት ይቻላል ከቆሻሻ እናፀዳለን። ይህን ማድረጋችን ደስየሚል ነገር ነው። ማሻአሏህ! ይሁን እንጂ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ውጫዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን ማፅዳት ያለብን ወንጀላችነንም ከልብ በመነጨች እና ጥርት ባለች ተውባ ማፅዳት ይኖርብናል።

ፆም ከንጋት አንስቶ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥ ፣ ከግብረ ስጋግንኙነት እና ሐራም ከሆኑ ነገሮች ሁሉ በመራቅ አሏህን ከምንገዛባቸው መመንገዶች አንዱ ነው። ፆም ፈርድ ሲሆን ከኢስላም መሠረታዊ ድንጋጌዎችም ነው።

አምላካችን አሏህ(ሱ.ወ.ተ) እንዲህ ይላል:-


App full proxy-5.php 30

=<({አል-ቁርአን 2:183})>=

Al-Quran-kareem 1

{183} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፈሪዎች(ሙተቆች) ትሆኑ ዘንድ ፆም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት ሕዝቦች ላይ እንደ እንደተደነገገው ሁሉ በናንተም ላይ ተደነገገ።

እንዲሁም በቡሐሪ እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-

ጥራዝ 1,መጽሐፍ 2,የሐ.ቁጥር7
ኢብኑ ኡመር እንደተረከው
የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ኢስላም በሚከተሉት አምስት መርሆዎች መሠረት ነው ብለዋል:-

1) ከአሏህ ውጭ ሊመለክ የሚገባው ነገር አለመኖሩንና ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር

2) ሶላት መስገድ

3) ዘካ መስጠት

4) ሐጅ ማድረግ

5) የረመዷንን ወር መፆም


App full proxy-5.php 31

የረመዷን ወር ትሩፋቶች


Ramadan poster

- የፆመኛ ሰው አፍሽታ ከሚስክ በላይ ለአሏህ አስደሳች ነው።

- መላኢካዎች ለሚፆም ሰው ፆሙን እስኪፈታ ድረስ የአሏህን ምህረት ይለምኑታል።

- በጀነት ባቡረያን የሚባል በራፍ ያለ ሲሆን በዚህ በራፍ ማንም አይገባም ፆመኞች ብቻ ሲቀሩ።

- አሏህ ሁለት የደስታ ጊዜያቶችን ያጐናፅፈናል። 1 ፆምን ስንፈታና 2 ከአምላካችን አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ስንገናኝ

- በረመዷን ወር ሸይጧኖች ይታሰራሉ።

- የረመዷን ወር በውስጡ ለይለቱል ቀድርን የያዘነው። ለይለቱል ቀድርም ከሽ ወራቶች በላይ በላጭ ነው።

- በረመዷን ምሽት መጨረሻ ላይ ፆመኞች ሃጢያታቸው ይማርላቸዋል።

- በእያንዳንዱ የረመዷን ምሽት አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ሰዎችን ከጀሐነም እሳት ያወጣቸዋል።

- በቅን እምነት እና ከአሏህ ዘንድ ምንዳ እንደሚያገኝ አስቦ በቀደር ምሽት ለሶላት የቆመ (የሰገደ) ያለፉት ሃጢያቶቹ ይማሩለታል።


App full proxy-5.php 32

የረመዷንን ወር እንዴት እንቀበለው

App full proxy-5.php 3310172685 321321404693425 5394365181197373228 n

- ከወዲሁ ኒያችነን እናስተካክል

- ረመዷንን ትክክለኛና ጥርት ባለች ተውባ እንቀበል

- አሏህ በሙሉ ጤንነት ያደርሰን ዘንድ ዱአ እናድርግ

- ጊዜያችነንም መልካምና ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን በመስራት እንዴት ማሳለፍ እንዳለብን ከወዲሁ እንቀድ

- ለምንሰራው ስራና ለእያንዳንዷ ሰዓታችን አትኩሮት እንስጥ

- ስራዎቻችነን አጥርተን እና አሳምረን ለአሏህ ብለን እንስራ

- ከመዲሁ መልካም ስራዎችን በመስራትና ሱና የሆኑ ነገሮችን አብዝተን እንተግብር

- ቁርአን አዘውትረን እንቅራ

- ትዕግስተኛ እንሁን

- ከማንኛውም አይነት ወንጀል እንራቅ

- ምላሳችነን ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንጠብቃት

- አህላቃችነን እናስተካካል

- የተጣላነው ሰው ወይም የበደል ነው ሰው ካለ አውፍ እንዲለን እንጠይቅ። እኛንም ያስከፋን ወይም ቅር ያሰኘን ሰው ካለ ለአሏህ ብለን አውፍ እንበለው።

- የሰዎችን ሐቅ እንመልስ

- ምላሳችንን በዚክር ፣ በዱአ ፣ በስቲግፋር ከወዲሁ እናለዝባት

- ምላሳችነን ከመጥፎ ነገር እንጠብቅ

- የተጣላ ሰው እናስታርቅ

- የተለያዩ መጽሐፎችን በማንበብና ዳዕዋዎችን በማድመጥ አእምሯዊና መንፈሳዊ ዝግጅት እናድርግ

- ሰዎች ለዚህ ታላቅ ወር ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናድርግ

اللهمَّ بلِّغْنا رَمَضَان.........

 By Ahmed Yesuf CEO and Founder of Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ

Like this page:
http://facebook.com/youth.mission29

website:
http://youth-mission.mobie.in

{.♥.° ኑ ስለ ኢስላም እንተዋወስ °.♥.}

'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_

©የወጣቱ ተልእኮ

App full proxy-3 18.php1
2004

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ